መረጃ

Your internet is very weak.
የእርስዎ ኢንተርኔት በጣም ደካማ ነው።
ናትካ ኢንተርነት ብዙሕ ደካማ እዩ።
nternet kee baaxô daciifa.
በትዕግስት ይጠብቁ!

loading 30-03-2026 22:08pm

የግዳን ወረዳ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት እና የሙጃ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በጋራ በመሆን።

የግዳን ወረዳ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ከሙጃ ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት ጋር በመተባበር ሙጃ ከተማን የበለጠ ለማሳደግ የሚያስችል የንቅናቄ መድረክ አካሄ ሙጃ፡ ቀን 02/11/2017ዓ.ም (ግዳን ወረዳ ኮሙኒኬሽን) በፕሮግራሙ የሰሜን ወሎ ዞን ህብረት ስራ ማህበራት ማስተባበሪያናማስፋፊያ ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሃብታሙ እባቡ፣ የግዳን ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማኑኤል አያሌዉ፣ የግዳን ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ባዩህ ፣ የወረዳው ስራ አስፈፃሚ አመራሮች ፣ የግዳን ወረዳ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰማኝ ቸኮለ፣የሙጃ ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘመድ ቢረዳ እና የወረዳዉ ጠቅላላ አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። የፕሮግራሙን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የግዳን ወረዳ ዋና አስተዳደሪ አቶ አማኑኤል አያሌዉ እንደተናገሩት የሙጃ ከተማ እድሜ ጠገብ ከተማ መሆኗን ጠቁመዉ የከተማዋን የአገልግሎት አሰጣጥ ዲጂታላዝድ እንዲሆንና የዘመነች ከተማ እንድትሆን ሁሉም አስተዋፅኦ ማበርከት እንዳለበት አሳስበዋል። የግዳን ወረዳ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰማኝ ቸኮለ እንደገለፁት የንቅናቄ መድረኩ ዓላማ የሙጃ ከተማን ላመሳደግ ምን ስራዎች እንደተሰሩ ፣ቀሪ ስራዎችስ ምን ምን ናቸዉ፣ከተማዋን በሚፈለገዉ ልክ ለማዘመን ከማን ምን ይጠበቃል የሚሉ ጉዳዮችን ለማስገንዘብ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ከተማዋን ወደ ከተማ አስተዳደር ለማሳደግ ብዙ መስፈርቶች አሉ ያሉት የጽ/ቤቱ ኃላፊ አሁን ላይ ሙጃ ከ4 እና ከ5 ቀበሌ በላይ የሚሆን የከተማ አደረጃጀት እንዳላት ጠቁመዉ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ለመሪ መዘጋጃ ቤቱ ድጋፍ ማድረግ አለበት ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡ የሙጃ ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘመድ ቢረዳ በበኩላቸዉ ይህ ፕሮግራም ሙጃን ለማሳደግ እያንዳንዱ አካል ኃላፊነት እንዲወስድና ችግሮች ካሉ መፍትሄ በመስጠት ወደ ስራ ለመግባት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለዉ ያሉ ሲሆን የሙጃ ከተማ ባለሃብቶች በገንዘባቸዉ እና በጉልበታቸዉ ተሳታፊ መሆን እና በመደራጀት አነስተኛ የስራ ዘርፎችን ከፍተዉ በስራ ዕድል ፈጠራዉ ላይ በትኩረት በመስራት ሙጃን እንዲያበለፅጉ ጥሪ አሳተላልፈዋል፡፡

ይህ ዘገባ የተነበበው 21ጊዜ ነው

Comment Form