በግዳን ወረዳ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የሙጃ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በሲስተሙ ላይ የተሰሩ ስራዎች የማጠቃለያ ሪፖርት

EISWD:25-10-2025 16:34pm

የግዳን ወረዳ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ከሙጃ ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት ጋር በመተባበር ሙጃ ከተማን የበለጠ ለማሳደግ የሚያስችል የንቅናቄ መድረክ አካሄደ ሙጃ፡ ቀን 02/11/2017ዓ.ም (ግዳን ወረዳ ኮሙኒኬሽን) በፕሮግራሙ የሰሜን ወሎ ዞን ህብረት ስራ ማህበራት ማስተባበሪያናማስፋፊያ ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሃብታሙ እባቡ፣ የግዳን ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማኑኤል አያሌዉ፣ የግዳን ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ባዩህ ፣ የወረዳው ስራ አስፈፃሚ አመራሮች ፣ የግዳን ወረዳ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰማኝ ቸኮለ፣የሙጃ ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘመድ ቢረዳ እና የወረዳዉ ጠቅላላ አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። የፕሮግራሙን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የግዳን ወረዳ ዋና አስተዳደሪ አቶ አማኑኤል አያሌዉ እንደተናገሩት የሙጃ ከተማ እድሜ ጠገብ ከተማ መሆኗን ጠቁመዉ የከተማዋን የአገልግሎት አሰጣጥ ዲጂታላዝድ እንዲሆንና የዘመነች ከተማ እንድትሆን ሁሉም አስተዋፅኦ ማበርከት እንዳለበት አሳስበዋል።